አል-ቁርዓን ትርጉም - Amharic Quran

CreativePro

አል-ቁርዓን ትርጉም - Amharic Quran

Books & Reference
  • 0.00
(0 投票)

免费安装

1000

应用安装

Android 5.0+

最低版本

带广告

广告

29.04.2022

发布日期

描述:

ከሃምሳ ዓመት በፊት በሸኽ ሙሐመድ ሳኒ ሃቢብ እና በሸኽ ሰይድ ሙሐመድ ሳዲቅ ወደ አማርኛ ቋንቋ ተተርጉሞ የቀረበው የክቡር ቅዱስ ቁርኣን የአማርኛ ትርጉም፤ እንሆ በወንድም ሙሐመድ ፈረጅ ድምፅ ተዘጋጅቶ በተለያዩ አጋጣሚዎች የቅዱስ ቁርኣንን ትርጉም ማድመጥ ለሚፈልጉ አመቺ ኾኖ ቀርቧል።

ይህ መጽሐፍ የመጀመሪያው ምዕራፍ መግቢያውና ሙስሊሞች በአጠቃላይ ቁርአን ከእግዚአብሔር መጣ የሚል እምነት እንዳላቸው የሚናገር ነው፡፡ ሙስሊሞች በሙሉ ያላቸው ይህ እምነትና መረዳት በሐቀኛ ምርመራ በመመሥረት የቁርአን ምንጭ ምንነት መገለጡ መከተል ያለባቸውን አሁኑኑ እንዲያስቡበት በጣም እንደሚረዳቸው ይታመናል፡፡

ቅዱስ ቁርአን ወይንም ቁርአን) የመሃከለኛዉ አለም የእስልምና የቅዱስ መጽሃፍ ወይም የእምነት ጽሁፍ ነዉ፣ በዚህም ትምህርት ይህ ጽሁፍ የመጣዉ በአላህ ፈቃድ ቃሉን በጂብሪል አማካኝነት ለነብዩ ሙሀመድ የወረደ የአላህ ቃል ነው። ቅዱስ ቁርአን ለመጀመርያ ጊዜ በአረብኛ ነበር የተጻፈዉ። አላህ ለቁራን ቃል ገብቶለታል እሱም ማነም ሰዉ መበረዝ እንደማይችል እና ማነም ሰዉ ቃሉን ቀይሮ ህጉን ሊአሳስት እንደማይችል ነዉ። አላህ ሁልጊዜም ከመበረዝ የሚጠብቀዉ በአለም ላይ ያለ ብቸኛው መጽሃፍ ነዉ። ይሀም በአማርኛ የተተረጎመ ቁርዓን ነዉ።

ቁርአን ሰዎች እና አጋንንት እንኳ ቢሰበሰቡ የሱብ ተመሳሳይ አንቀጽ ወይም አረፍተ ነገር ማምጣት ይችሉ እንደሆነ ይሞክሩ በማለት ተአምረኛነቱን እና እውነተኛነቱን አረጋግጧል። ቁርአን ከመበዘረዝ እና ከመከለስ የጠራ ነው። እንደዚህም የሰው ልጆች ሁሉ መመሪያ እንደሆነ ሳይበረዝ እና ሳይከለስ እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ይቆያል፤ ምክንያቱም አላህ እጠብቀዋለሁ ብሎ ቃል ስለገባለት ቁርአንን በተመለከተ ሙስሊሞች ምንም አይነት ልዩነት የለባቸውም። በአረብኛ ተጽፎ አንድ ቃል ይቅርና አንድ ፊደል እንኳ ሊጨመር ቢችል ወይም ቢቀነስ በቀጥታ በቀላሉ ማወቅ ይቻላል። የሰው ልጆች በዚህ ምድርም ይሁን በመጭው አለም ሰላም እና እርጋታ ከፈለጉ ሙስሊም ሆነው በቁርአን መመራት አለባቸው የሚል ትምህርት ያቀርባል።


የድምፅ ሥራው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ በቅርቡ በዚህ መተግበሪያ እስኪጫን ድረስ፤ ለጊዜው ሱረት አል ፋቲሃን ጨምሮ ከሱረቱ አን ናስ እስከ ሱረቱ አን ነበእ (አንድ ጁዝ) የትርጉም ድምፅ ሥራው ያለክፍያ ቀርቧል።

በዚህ አጋጣሚ እንደ አላህ ፈቃድ ሥራችንን ከእንከን የጠራ ለማድረግ በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜትና ጥንቃቄ ጥረት ያደረግን ቢኾንም፤ ሰዎች ነንና ልንሳሳት እንደምንችል እናምናለን። በመኾኑም ይህ ሥራ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሸጋገር የቅዱስ ቁርአን ትርጉም እንደመኾኑ በማድመጥም ኾነ በማንበብ ሂደት ውስጥ የሚታያችኹን ክፍተት እንድተጠቁሙን በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን።

ይህን ታላቅ ሥራ አኑረው ያለፉ አባቶቻችንንና ከህትመት እስከ ስርጭት የደከሙ ወንድምና እህቶችን ኹሉ ለሠሩት መልካም ሠራ ምንዳውን ያብዛላቸው። እኛንም በሰማነው የምንጠቀም ያድርገን። አሚን!!

CreativePro 其他应用

下载